የነገረፈጁ ስልጣን

መተግበሪያ አውርድ

የሰነድ ማረጋገጫ እና ህጋዊነት

መተግበሪያ አውርድ

About Us

Initially, this technology was created to change each and every service given at the Ethiopian embassies all over the world in to a full digital system. By doing so, we hope to give a convenient and pleasant experience for anyone that requires service from any Ethiopian embassy or consular offices. Moreover, we expect this technology to bring economic benefit back home. As a government representative our first priority would be to empower our people, wherever they maybe by providing them the best service. Ultimately, we long Ethiopia to become an easy and favorable destination for investment, tourism and other various fields.

ተልዕኮ!

ተልዕኳችን ደህንነቱ የተጠበቀ ፈጣንና አስተማማኝ የዲጂታል ኢምባሲና ቆንጽላ አገልገሎቶችን በዓለም ዙሪያ ለሚገኙ ኢትዮጲያውን እና ትውልደ ኢትዮጲያውን በተመጣጣኝ ዋጋ ማቅረብ ነው!

ራዕያችን!

በኢፌድሪ ውጪ ጉዳይ መስሪያ ቤት ስር በዓለም ዙሪያ በኢምባሲና ቆንጽላ ጽህፈት ቤት በኩል የሚሰጡ ማናቸውንም አይነት አገልግሎቶችን ሙሉ በሙሉ ወደ በይነመረብ አገልግሎት መስጫ አማራጮች መቀየር ነው!
ይህንን የቴክኖሎጂ አማራጭ ለማቅረብ ስንነሳ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የኢትዮጲያ ኢንባሲና የቆንጽላ ጽህፈት ቤቶች አማካኝነት የሚሰጡ ማናቸውንም አይነት አገልግሎት ሙሉለሙሉ ወደ ዲጂታል የአገልግሎት አማራጮች ለመቀየር ነው! ይህም ለማንኛውም የኢንባሲና የቆንጽላ ጽህፈት ቤት አገልግሎት ፈላጊ ደምበኛ ፈጣን እና ቀልጣፋ አገልግሎትን ለመስጠት ያስችለናል ብለን እናምናለን። ከዚህም በተጨማሪ ዓለም የደረሰበትን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ አማራጮችን ለደምበኞቻችን ማቅረብ ሀገራችንን ለቱሪዝም፣ ኢቨስትመንት እና ሌሎች ዘርፎች ተመራጭ እንድትሆን በማድረግ ለሀገራችን ሁለንተናዊ እድገትና ብልፅግና ከፍተኛ አስተዋጾ ያደርጋል ብለን እናምናለን።

ሙሉ በሙሉ በበይነመረብ አማካኝነት የሚሰጥ የኢምባሲ አገልግሎት ጥቅሞች

ማህበራዊ ተሳትፎ: ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በሀገርዎ ላይ በተለያየ መልኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይበረታታሉ

የውጭ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት

ፈጣንና ቀልጣፋ አገልግሎቶችን በሚያገኙበት ጊዜ በሀገርዎ ላይ በተለያየ መልኩ ተሳታፊ እንዲሆኑ ይበረታታሉ

ማህበራዊ ተሳትፎ

በአካል ኢትዮጵያ መሄድ ሳይጠበቅቦት በሀገርዎ ላይ ኢንቨስት ማድረግ ይችላሉ

የንግድ ጥቅም

አዲሱ የዲጂታል ሞፋ ቴክኖሎጂ ባለ ብዙ አማራጭ ነው

የዝውውር መጠን

እንዲህ ያሉ ፈጣንና ቀልጣፋ የቴክኖሎጂ አማራጮች ብዙ ደንበኞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ እንዲሆኑ ያብረታታል ይህም በሀገራችን ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ተጽኖ ይኖረል

ውክልናን ለመስጠት የሚያስፈልጉ ሰነዶች

  • የመኖሪያ ፍቃድ
  • ፓስፖርት
  • የመንጃ ፍቃድ
  • የመኖሪያ ፍቃድ
  • ስቴት አይዲ
  • የሎ ካርድ
  • የውትድርና መታወቂያ

Awesome Image

የምንሰጣቸው አገልግሎቶች

ውክልና አገልግሎቱ በውጪ ሀገራት የሚገኙ ኢትዮጲያውያን እና ትውልደ ኢትዮጲያውያን በተለያዩ ምክንያቶች ከሀገር ቢወጡም ከሀገር አንዳይርቁ ያግዛል። ከዚህ ቀደም በነበረው የውክልና አሰጣት ሂደት ተገልጋዮችን ለብዙ እንግልት የዳረገና አገልግሎቱንም ለማግኘት ከሰላሳ ቀናት በላይ ይፈጅ የነበረ ሲሆን አዲሱና በሞባይል መተግበሪያ አማካኝነት የሚሰጠው አገልግሎት እንደ የንብረት አስትዳደርን፣ መሸጥ መለወጥን፣ የፍርድ ቤት እና ሌሎች በሀገርቤት ያሉ ጉዳዮችን በውክልና ለማስፈጸም ይረዳዎት ዘንድ ውክልናን ለሚፈልጉት አካል ከ24-48 ሰዓታት ውስጥ ሀገርቤት እንዲልኩ ያስችሎታል!

ከሀገር ውጭ ወደ ሀገር ውስጥ

ደንበኞች ባሉበት ሃገር ህጋዊነቱ የተረጋገጠውን ሰነድ በሀገር ውስጥ ለሚፈልጉት አላማ ለማዋል በኢፌድሪ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ በኩል ህጋዊነቱ ተረጋግጦ የሚያፍበት ሂደት ሲሆን! አገልግሎቱን ለማግኘትም መተግበሪያውን በማውረድ አካውንት በመክፈት የሚጠየቁትን መጠይቆች በመሙላት ህጋዊነቱ እንዲረጋገጥ የሚፈልጉትን ሰነድ ስካን በማድረግ ካስገቡ በሁዋላ ቀጣይ መጠይቆችን በመሙላት ያጠናቅቃሉ:: በመጨረሻም ያስገቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነትና ህጋዊነት በኢትዮጲያ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተረጋግጦ ከ24-48 ሰዓታት ውስጥ አዲስ አበባ በሚገኘው የውጪጉዳይ ቆንጽላ ጽ/ቤት ቢሮ በመገኘት እርሶ ወይንም የወከሉት አካል በአካል ተገኝተው ሰነዶን በመውሰድ ለሚፈልጉት አላማ ማዋል ይችላሉ፡፡

Learn more about the Process
Awesome Image

ከሀገር ውስጥ ወደ ውጪ ሀገራት

ደንበኞች በሀገር ውስጥ በኢትዮጲያ መንግስት በኩል ህጋዊነቱ የተረጋገጠ ሰነድን በውጪ ሀገራት ጥቅም ላይ ለማዋል በኢፌድሪ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ በኩል ህጋዊነቱ ተረጋግጦ የሚያፍበት ሂደት ነው። አገልግሎቱን ለማግኘትም መተግበሪያውን በማውረድ አካውንት በመክፈት የሚጠየቁትን መጠይቆች ከሞሉ በሗላ ህጋዊነቱ እንዲረጋገጥ የሚፈልጉትን ሰነድ ስካን በማድረግ ያስገባሉ:: ቀጣይ መጠይቆችን በመሙላት ያጠናቅቃሉ በመጨረሻም ያስገቧቸውን ሰነዶች ትክክለኛነትና ህጋዊነት በኢፌድሪ የውጪጉዳይ ሚኒስቴር ቢሮ በኩል ህጋዊነቱ ተረጋግጦ በሚኖሩበት ሀገር አድራሻ ከ24-48 ሰዓታት ውስጥ ይላክሎታል!

Learn more about the Process
Awesome Image

Happy Applicants for Digital Experience